Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ዛሬ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ዛሬ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው።
የአዲስ አበባን የአውራ ጎዳና መንገዶችን ተከትሎ እየተካሄደ ባለው የኢፍጣር መርሃ ግብር ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እየተሳተፉበት ነው።
የተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ ታላላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሃ ግብር ሲያዘጋጁ ቆይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ኢድን በአገር ቤት እናክብር በማለት “ታላቁ የኢድ ሰላት በኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል ለኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ለኢትዮጵያ ወዳጆች ጥሪ ማቅረባቸውን ተከትሎ የገቡ እንግዶችም በዛሬው የኢፍጣር መርሃ ግብር ላይ እየተሳተፉ መሆኑም ተገልጿል።
በአብረሃም ፈቀደ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.