Fana: At a Speed of Life!

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለሦስት ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ለሦስት ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ዛሬ ሚያዚያ 27 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ዶክተር ዋሴ ሞላ፣ ዶክተር ካሳሁን ዓለሙ እና ዶክተር ሰሎሞን መኮንን ወደ ሙሉ ፕሮፌሰርነት እንዲያደጉ ወስኗል፡፡
ቦርዱ የሦስቱን ምሁራን መረጃ መርምሮ ዕድገቱ እንደሚገባቸው አረጋግጧል።
በመሆኑም በመማር ማስተማር፣ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምሁራኑ ያበረከቱት አስተዋጽኦ የደረጃ ዕድገቱን እንዲያገኙ አስችሏል መባሉን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.