Fana: At a Speed of Life!

ኮሮና ቫይረስ በሰሜን ኮሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ ተገኘ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ኮሪያ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ መገኘቱን የሃገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ አስታወቀ።

በሃገሪቱ የተገኘው የኮሮና ቨባይረስ ዝርያ አዲሱ የአሚክሮን ቫይረስ ሲሆን፥ የቫይረሱን መገኘት ተከትሎም ጥብቅ የሆነ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉ ተገልጿል።

የሀገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ ኡን የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በመላው ሀገሪቱ ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲታወጅ አዘዋል ነው የተባለው።

የሃገሪቱ የቴለቪዥን ጣቢያም ላለፉት ሁለት አመታት ጥበቃ የተደረገበት የድንገተኛ ወረርሽኝ መከላከያ መጣሱን ዘግቧል።

ላለፉት ሁለት አመታት የበርካታ ሃገራትን ኢኮኖሚ ያናጋው ኮሮና ቫይረስ በሰሜን ኮሪያ ከዚህ ቀደም ተከስቶ እንደማያውቅ አር ቲ እና ቢቢሲ በዘገባቸው አስታውሰዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.