Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለተመራጩ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት የእንኳን ደስ ያልዎት መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለተመራጩ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ የእንኳን ደስ ያልዎት መልዕክት አስተላለፉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በደስታ መግለጫቸው፥ ከፕሬዚዳንት ሞሀመድ ጋር ለኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የጋራ በሆኑ ሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ተቀራርበው በጋራ እንደሚሰሩም እምነታቸውን ገልፀዋል።
የሶማሊያ ፓርላማ ሀሰን ሼክ ሞሀመድን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አድርጎ መምረጡ ይታወቃል።
ትናንት በተካሄደው ምርጫ የመጨረሻ ድምፅ አሰጣጥ ሞሀመድ ስልጣን ላይ የነበሩትን መሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆን በማሸነፍ ነው የተመረጡት።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.