ጠንካራ ሀገር ለመገንባት ሀገራዊ ችግሮችን በምክክርና በመነጋገር መፍታት ያስፈልጋል- ዶክተር ይልቃል ከፋለ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠንካራ ሀገር ለመገንባት ሀገራዊ ችግሮችን በምክክርና በመነጋገር መፍታት እንደሚያስፈልግ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ገለጹ፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር የትውውቅ መርኃ ግብር እያካሄደ ነው።
በመድረኩ ላይ ዶክተር ይልቃል ከፋለን ጨምሮ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ፣ የኮሚሽኑ አባላት፣ ከአማራ ክልል የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች፣ እናቶች እና ወጣቶች ተገኝተዋል።
ልዩነትን በማጥበብና በመቻቻል የተመሠረተች ጠንካራ ሀገር እንድትኖር የአማራ ክልል መንግሥት ከሀገራዊ ምክክሩ ጎን በመኾን አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ዶክተር ይልቃል ከፋለ መግለጻቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ኮሚሽኑ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚለያዩንን አጀንዳዎች ለመቀነስ እና አንድነትን ለማጠናከር አልሞ የተቋቋመ ነው ብለዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-