ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ ከቻይናው የኢኮኖሚ ጉዳዮች ኮንሱላር ያንግ ዪ ሃንግ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ ከቻይናው የኢኮኖሚ ጉዳዮች ኮንሱላር ያንግ ዪ ሃንግ ጋር በኢትዮጵያ ኢንቨስት የሚያደርጉ ቻይናውያን ባለሀብቶችን ቁጥር ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡፡
በውይይታቸውም÷ በቅርቡ በኢንቨስትመንቱ ዘርፉ አብሮ ለመስራት በቻይና የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ኤጀንሲ እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ የአፈጻጸም ሂደት ላይ መክረዋል፡፡
የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ዕድል እና አማራጮች በሰፊው ለቻይና ባለሀብቶች የማስተዋወቁን ስራ በሰፊው ለመስራት እና የቻይና ባለሀብቶችን ቁጥርም ለማሳደግ ከስምምነት መደረሱን የኮሚሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡
በአፈጻጸም ጊዜ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶችን አፋጣኝ መፍትሔ የሚሰጡ የድጋፍ እና ክትትል ስራዎች ላይም ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!