Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ለኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች 22 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ብድር ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2014 በጀት ዓመት በአማራ ክልል የሚገኙ የግልና የመንግስት ባንኮች በተለያዩ የብድር ሞደሊቲዎች 22 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ብድር ለኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች መሰጠታቸው ተገለፀ፡፡

ለረዥም ጊዜ የክልሉ ችግር ሆኖ የቆየው የፋይናንስ ብድር አቅርቦት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ መሻሻል እያሳየ መምጣቱ ተገልጿል፡፡

በመሆኑም በ2014 በጀት ዓመት ለ114 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች 11 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር የፕሮጀክት ፋይናንስ ብድር፣ለ367 ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች 933 ሚሊየን ብር የሊዝ ፋይናንስ፣ እና ለ150 ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ደግሞ 10 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር የሥራ ማስኬጃ ብድር በድምሩ ለ631 ፕሮጀክቶች 22 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ብድር አግኝተዋል፡፡

በዚህም ቀደም ባሉት ዓመታት ከነበሩት አፈፃፀሞች አንፃር ከፍተኛ መሻሻል እያሳየ እንደሆነ የሚያሳይ ቢሆንም በክልሉ ካሉ ብድር ፈላጊ ፕሮጀክቶችና ባንኮች ከክልሉ ከሚሰበስቡት ገቢ አንፃር ገና ብዙ መስራትን የሚጠይቅ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪ በዘርፉ ያለው የውጭ ምንዛሬ እጥረትና የአሰራር ግልፀኝነት መጓደል መስተካከል ይኖርባቸዋል መባሉን ከክልሉ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.