Fana: At a Speed of Life!

ሳውዲ ዓረቢያ 3 የዝንጀሮ ፈንጣጣ  ቫይረስ ተጠቂዎች መገኘታቸውን ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳውዲ ዓረቢያ ሦስት  የዝንጀሮ ፈንጣጣ  ቫይረስ ተጠቂዎች መገኘታቸውን የሀገሪቱ  ጤና  ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የሀገሪቱ የጤና  ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በሰጡት መግለጫ፥  ቀደም ሲል አንድ የዝንጅሮ ፈንጣጣ ቫይረስ ተጠቂ መገኘቱን አስታወሰው፥ የዛሬዎቹን ሁለቱን ጨምሮ በአጠቃላይ በሀገሪቱ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ የተገኘባቸው ዜጎች ቁጥር ወደ ሦስት ከፍ ማለቱን አረጋግጠናል ብለዋል።

ሦስቱም ቫይረሱ የተጠቁት ሰዎች ከአውሮፓ የመጡ መሆናቸውንም ቃል አቀባዩ ይፋ አድርገዋል።

የመጀመሪያው የቫይረሱ ተጠቂ በፈረንጆቹ ሐምሌ 14 በሪያድ የተገኘ ሲሆን ግለሰቡ ከሳውዲ አረቢያ ወደ አውሮፓ ጉዙ አድርጎ እንደነበር ነው የጠና ሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ የተናገሩት፡፡

ሚኒስቴሩ በዛሬው ዕለት የተመረመሩት የዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ  ተጠቂዎች ከአውሮፓ ጉዙ አደርገው የተመለሱ ናቸው ማለቱን አራብ ኒውስ ዘግቧል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት የዝንጀሮ ፈንጣጣ  የዓለማችን አስጊ በሸታ  እንደሆነ ማወጁን  በቅርቡ ዘግበናል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.