Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ 60 በመቶ ሴት ወጣቶች በሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ይሆናሉ – አቶ ጃንጥራር ዓባይ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ 60 በመቶ ያህል ሴት ወጣቶች በወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የሥራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር ዓባይ ተናገሩ፡፡
አቶ ጃንጥራር ዓባይ ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ በብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት 60 በመቶ ያህል ሴት ወጣቶች ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል፡፡
በመጀመሪያው ምዕራፍ በተመረጡ 36 ወረዳዎች 10 ሺህ 500 ወጣቶችን በፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ሥራ መከናወኑን ገልፀው÷ እስካሁን በ36 ወረዳዎች 27 ሺህ 297 ወጣቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል፡፡
በመጀመሪያው ዙር ተጠቃሚ የሚሆኑ ወጣቶች ከነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ገብተው እየሰለጠኑ መሆኑም ተገልጿል፡፡
ወጣቶቹን ተቀብለው ሊያሰለጥኑ የሚችሉ 1 ሺህ 505 ድርጅቶችን የመለየት እና ለ378 አሰልጣኞች ሥልጠና መሰጠቱን የሥራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወጣቶቹ ከስልጠና በኋላ በተለዩ ድርጅቶች ገብተው ለስድስት ወር የሥራ ላይ ልምምድ ያደርጋሉ ተብሏል፡፡
ፕሮጀክቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ 70 ሺህ እንዲሁም በአዲስ አበባ ደግሞ 49 ሺህ ወጣቶችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.