Fana: At a Speed of Life!

10ኛው የበጎ ሰው ሽልማት መርሐግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 10ኛው የበጎ ሰው ሽልማት መርሐግብር በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል እየተካሄደ ነው።

መርሐግብሩ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

በጎ ሰሪዎችን እውቅና በመስጠት ሌሎች በጎዎችን መፍጠር አላማ ያደረገው ይህ መርሐግብር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ለሀገር እና ለወገን መልካም ለሰሩ እና በጎ ለዋሉ ሽልማትና እውቅና የሚሰጥበት ነው።

መርሐግብሩ እስካሁን በነበሩ አመታት 187 በጎ ሰዎችና ድርጅቶችን እውቅና ሰጥቷል።

የመምህርነትን እና መንግስታዊ ሃላፊነትን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ነው ሽልማቱ የሚሰጠው።

ለዚህኛው ሽልማትም 691 እጩዎች ለዘርፎቹ የቀረቡ ሲሆን፥ ለየዘርፎቹ የመጨረሻዎቹ ሶስት እጩዎች መለየታቸው ተገልጿል።

ሀብታሙ ተክለስላሴ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.