ፋሲል ከነማ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ከቡሩንዲው ቡማሙሩ ጋር ዛሬ ያደርጋል
አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋሲል ከነማ የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ከብሩንዲው ቡማሙሩ ጋር ዛሬ ያደርጋል፡፡
የሁለቱ ክለቦች የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ከቀኑ 9 ሰአት ላይ የሚደረግ ይሆናል።
በፋሲል ከነማ በኩል ሀብታሙ ተከስተ በህመም ምክንያት ከዛሬው ጨዋታ ውጭ ሲሆን ከካፍ ጨዋታዎች የተመለሱት ሚካኤል ሳማኪ፣ ከድር ኩሊባሊ እና አዲሱ ፈራሚ ጋራን ጆፋ በዛሬው ጨዋታ ይሰለፋሉ ተብሏል።
የመሀል ተከላካዩ አስቻለው ታመነ ቡድኑን በአምበልነት እንደሚመራ ከክለቡ ያገኘነው መረጀ ያመላከታል፡፡
ፋሲል ከነማ የመልስ ጨዋታቸውን መስከረም 6 ቀን 2015 ዓ.ም የሚያደርግ ሲሆን በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈ በቀጣዩ ዙር ከቱኒዚያው ሰፋክሲያን ጋር የሚጫዎት ይሆናል፡፡