የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለጤናማ ህይወት
አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ጤናማ ህይወትን ለመምራት ያስችላል፡፡
መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ከሚሰጠን ዘርፈ ብዙ የጤና በረከቶች ውስጥ የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
ክብደትን ለመቀነስ ዋነኛ መፍትሄ ሲሆን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በሚደረግበት ጊዜ በሰውነት ላይ የሚገኙ ስቦችን በማቅለጥ የካሎሪ መጠን እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡
የክብደት መቀነስን ለመከላከል የሚረዳ ሲሆን፥ መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የክብደት መቀነስ የሚያስከትለውን የካሎሪ መጠን እንዲስተካከል ያደርጋል፡፡
ከዚህ ባለፈም መደበኛ የአከል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የልብ እና የስኳር በሽታ ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ የዓለም አቀፉ የበሽታዎች መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል መረጃ ያመላክታል፡፡
በአጠቃላይ መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
የተስተካለ ውፍረት እንዲኖር እና ኃይልና ብርታት ለማግኘት
የደም ግፊትን ለማስተካከል
የልብ ድካም፣ የጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ እና የካንሰር ተጋላጭነትን ይቀንሳል
መገጣጠሚያ ላይ የሚከሰቱ እብጠቶች እንዳይከሰቱ
የአጥንት መሳሳት እና ራስን መሳት ችግሮች ለመከላከል
የመንፈስ ጭንቀት እና ድብርትን ለማስወገድ ይረዳል።
በቀን ለ30 ደቂቃ ወይም በሳምንት ለ150 ደቂቃዎች የኤሮቢክስ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ጤናማ ህይወትን ለመምራት ያስችላል፡፡