Fana: At a Speed of Life!

የዓየር ንብረት ለውጥ በጤና እና በዕፅዋት ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓየር ንብረት ለውጥ በሰው ልጆች ጤና እና ከግማሽ በላይ በሚደርሱ የከተማ ዕፅዋት ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን አንድ ጥናት አመላከተ፡፡

ጥናቱ ከተማ ውስጥ ለተተከሉ የዛፍ ዝርያዎች ክብካቤ እንዲደረግ እና በቀጣይ ድርቅን መቋቋም የሚችሉ ዕፅዋት እንዲተከሉ መክሯል፡፡

ከተማ ውስጥ የተተከሉ ዛፎች ቀዝቃዛ የዓየር ንብረት እንዲኖርና በጥላቸው ለኑሮ ምቹ ከባቢ እንዲፈጠር የጎላ ሚና እንዳላቸው ተመላክቷል፡፡

የከተማ እና የጎዳና ዛፎች የሰዎችን አካላዊ እና አዕምሯዊ ጤና በማሻሻል ረገድ ሚናቸው የጎላ በመሆኑ በማኅበራዊ ዑደት ውስጥ አስፈላጊ ናቸው ተብሏል፡፡

በአውስትራሊያ ፔንሪት የምዕራብ ሲድኒ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ የሆኑት ማኑኤል ኢስፔሮን-ሮድሪጌዝ እንደሚሉት፥ በዓየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ሙቀት በመጨመሩ እና የአፈር እርጥበት በመቀነሱ በከተማ ውስጥ የተተከሉት ዛፎች መድረቅ አደጋ ተጋርጦባቸዋል፡፡

በጥናት ከተካተቱት ከተሞች ውስጥ ለንደን ትገኝበታለች ነው የተባለው፡፡

ጥናቱ በ78 ሀገራት የሚገኙ 164 ከተሞችን ያካተተ ሲሆን ከ4 ሺህ በላይ የዛፍ እና የቁጥቋጦ ዝርያዎች ላይ ትኩረቱን አድርጓል፡፡

በውጤቱም ከ4 ሺህዎቹ ዝርያዎች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የመድረቅ አደጋ ላይ እንደሚገኙ ነው ቢቢሲ በዘገባው ያመላከተው፡፡

ዛፎች የዓለም የሙቀት መጨመርን ተፅእኖ በመቀነስ ረገድ የጎላ ሚና አላቸው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.