Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ለ300 ሺህ ተጠባባቂ ጦሯ ጥሪ ልታደርግ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ለ300 ሺህ ተጠባባቂ ጦሯ ጥሪ ልታደርግ መሆኑን የመከላከያ ሚኒስትሩ ሰርጌ ሾይጉ አስታወቁ።

ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሩሲያ “ከፊል ወታደራዊ ቅስቀሳ” እንዲደረግ ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በዛሬው እለት እንዳስታወቁት ወታደራዊ ቅስቀሳው ወታደራዊ ልምድ ያላቸው እና በተጠባባቂነት የሚገኙ ሃይሎች የሩሲያን ጦር እንዲቀላቀሉ የሚያደርግ ነው።

ፑቲን ሀገራቸው በመላው ምዕራባውያን ከምትደገፈው ዩክሬን ጋር ጦርነት ውስጥ ናት ብለዋል በሰጡት መግለጫ።

ወታደራዊ ቅስቀሳው የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ላለባት የተራዘመ ጦርነት ተጠባባቂ ሀይሎችን በሰራዊቱ ዕዝ ውስጥ ለማስገባት መወሰኑን ተከትሎ የመጣ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

ከሁኔታዎች አንፃር ወሳኔው ትክክል ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ ወታደራዊ ቅስቀሳው በፍጥነት እንዲጀመር ትዕዛዝ መስጠታቸውንም አብራርተዋል፡፡

ፑቲን በመግለጫቸው ምዕራባውያን በዚህ ሁኔታ ከቀጠሉ ሩሲያ ኒውክሌርን ጨምሪ ማንኛውንም አማራጭ እንደምትጠቀም አስጠንቅቀዋል።

የመከላከያ ሚኒስትሩ ሰርጌ ሾይጉ በበኩላቸው ለዩክሬን ጦርነት ለ300 ሺህ የተጠባባቂ ሀይሎች ጥሪ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

ጥሪ የሚደረግላቸው ዜጎችም ተጨማሪ ስልጠናዎችን እንደሚወስዱና በወታደራዊ ግዳጅ ላይ ያለው ሰራዊቱ የሚያገኘውን ጥቅማ ጥቅም እንደሚያገኙም ጠቁመዋል።

ቅስቀሳው በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደማይተገበር እና የውትድርና ልምድ ያላቸው ሩሲያውያን ብቻ ጥሪ እንደሚደረግላቸው መናገራቸውን አር ቲ እና ሞስኮ ታይምስ ዘግበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.