ለመከላከያ ሠራዊት ከ5 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ዞኖች ለመከላከያ ሠራዊት ከ5 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የአይነት ድጋፍ አደረጉ፡፡
የአዊ ብሔረሰብ አስተዳዳር ዞን ያሰባሰበውን ከ5 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ በሰቆጣ ከተማ ለሠራዊቱ አስረክቧል፡፡
እንዲሁም በሰሜን ወሎ ዞን የአንጎት ወረዳ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሠራዊት ግንባር ድረስ በመሄድ የስንቅ ድጋፍ ማድረጋቸውን የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡
በተመሳሳይ በምዕራብ ኦሞ ዞን የማጂ ወረዳ ለመከላከያ ሠራዊት 651 ሺህ 653 ብር ግምት ያለው የገንዘብና የአይነት ድጋፍ ማድረጉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ይጠቁማል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!