Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከብሪታንያ የልማት ሚኒስትርና ከሞዛምቢክ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከብሪታንያ የልማት ሚኒስትር ቪኪ ፎርድ እና ከሞዛምቢክ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማኑዌል ጎንቻልስ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

እንዲሁም የሀገራቱን ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይም ተወያይተዋል፡፡

አቶ ደመቀ ከብሪታንያ የልማት ሚኒስትር ጋር ባደረጉት ውይይት÷ በድርቅና በግጭት ለተጎዱ ወገኖች ሰብዓዊ ድጋፍ ማፋጠን በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ከሞዛምቢክ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በነበራቸው ውይይት ደግሞ÷ ኢትዮጵያ ሞዛምቢክ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አዲስ ተለዋጭ አባል ሆና አዎንታዊ ሚና እንደምትጫወት ትታምናለች ብለዋል።

ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማኑዌል ጎንቻልስ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ሞዛምቢክ እንድትመረጥ ላደረገችው ድጋፍ አመስግነው፥ “ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔዎች” በሚለው መርህ መሰረት የአፍሪካን ጉዳዮች ለመደገፍ ቃል ገብተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.