Fana: At a Speed of Life!

በአቃቂ ቃሊቲ የእሳት አደጋ የሰው ህይወት አጠፋ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ሌሊት 7 ሰዓት ከ44 ደቂቃ ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ወረዳ 13 ቱሉዲምቱ አካባቢ የተለያዩ አነስተኛ የንግድ አገልግሎት የሚሰጡ 15 የሚሆኑ በላስቲክ፣ በሸራና አነስተኛ ቁሳቁስ ተሰሩ መጠለያዎች በእሳት አደጋ ወደሙ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዕሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬት እንዳስታወቁት፥ እሳቱ ወደሌላ ስፍራ ሳይዛመት በቀላሉ መቆጣጠር ተችሏል።

በዚህ ሂደትም አምስት ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ከአደጋዉ ማዳን ተችሏል ነው ያሉት።

ይሁን አንጂ ከእነዚህ ሱቆች መካከል በመጽሀፍት ንግድ ላይ የሚሰራ እድሜው 32 ዓመት የሆነ ሰው በሱቁ ውስጥ እንደተኛ ህይወቱ ያለፈ ሲሆን፥ 300 ሺህ ብር የሚገመት ንብረትም ወድሟል።

እሳቱን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠርም አንድ ሰዓት ወስዷል።

እሳቱ ህይወቱ ካለፈው ሰው ክፍል ውስጥ መሆኑንና የአደጋው መንስኤ በፖሊስ እየተጣራ እንደሆነና አቶ ንጋቱ ተናግረዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.