Fana: At a Speed of Life!

የ “ብሩህ አይሲቲ ፈጠራ ውድድር” ማጠቃለያና የሽልማት መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ “ብሩህ አይሲቲ ፈጠራ ውድድር” ማጠቃለያና የሽልማት መርሐ ግብር በመካሄድ ላይ ነው፡፡

ውድድሩን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት እና የኢትዮጵያ ኢንተርፕርነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት ናቸው በጋራ ያዘጋጁት፡፡

መርሐ ግብሩ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ንጉሱ ጥላሁን በተገኙበት ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

በመርሐግብሩም እንደሀገር በተደረገው ጥሪ ለውድድር ቀርበው ለመጨረሻ ዙር የደረሱ 20 ተወዳደሪዎች ተካፍለዋል።

በተለያየ ዘርፍ የማህበረሰብን ችግር ይፈታሉ ተብለው በቴክኖሎጂ ታግዘው የቀረቡ የፈጠራ ሐሳቦች ውድድር አድርገዋል።

በሀብታሙ ተ/ስላሴ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.