Fana: At a Speed of Life!

ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ አብሮነት፣ ትብብር እና ልማት ላይ እንዲያተኩር ቻይና ጠየቀች

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ልማት ላይ ትኩረት አድርጎ የአብሮነት እና ትብብር መንፈሱን እንዲያሳድግ በተመድ የቻይና ምክትል ቋሚ ተወካይ ዳይ ቢንግ ጠየቁ፡፡

ዳይ ቢንግ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት በ77ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ መሆኑን ሲጂቲ ኤን ዘግቧል፡፡

ዳይ ቢንግ በመድረኩ በዓለምአቀፍ ደረጃ የሚስተዋሉ የማኅበራዊ ፣ ሰብዓዊ እና የመብት ጉዳዮችን በተመለከተም አንስተው መዳሰሳቸው ነው የተገለጸው፡፡

ዳይ ቢንግ ልማት ለሠላም እና መረጋጋት መሠረት መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ችግሮችን ለመፍታትም ልማት ቁልፍ ሚና አለው ብለዋል፡፡

ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ÷ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ፣ ቀጣናዊ ግጭቶች ፣ የምግብ ዋስትና ፣ የኃይል አቅርቦት፣ የዓየር ንብረት ለውጥ እና የመሳሰሉ የተወሳሰቡ ጉዳዮች ላይ በትብብር መሥራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

ያደጉ ሀገራት ልምዳቸውን ለታዳጊ ሀገራት በማካፈል እንዲሁም የዕድገት ግብዓቶችን በማቅረብ እና በመደገፍ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል፡፡

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የልማት ጉዳይን ዋና እና አንገብጋቢ ጉዳዩ አድርጎ እንዲመለከተውም አሳስበዋል፡፡

ልማትን ዕውን ለማድረግ የዓለምአቀፉን ማኅበረሰብ የተቀናጀ የፖሊሲ ትብብር እና ትግበራ አጋርነት ማስፋፋት እንደሚያሻም ዳይ ቢንግ ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.