Fana: At a Speed of Life!

የትምህርት ሚኒስቴር እና የሰላም ሚኒስቴር በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር እና የሰላም ሚኒስቴር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ ።

ስምምነቱን የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱ አለም እና የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተፈራርመውታል፡፡

ስምምነቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶቹ በዘላቂ የሰላም ግንባታ ላይ በጋራ መስራት የሚያስችላቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡

አቶ ብናልፍ አንዱአለም ÷ ሰላም ማለት ግጭትን እና ጦርነትን ማስወገድ ብቻ ሳይሆን የእነዚህ አደጋዎች መነሻ ምክንያት የሆኑ የውስጥ ችግሮችንም መፍታት ነው ብለዋል ፡፡

በኢትዮጵያ ያሉ የትምህርት ተቋማት ላይም እንዴት ተቀናጅተን ስለሰላም እንስራ የሚለው ላይም ስምምነቱ አቅም ይሆናል ተብሏል ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፈሰር ብርሃኑ ነጋ በበኩላቸው ÷ መሰል ስራዎች ዛሬ ለሚፈጠሩ ችግሮች እንኳ መፍትሄ ባይሆኑ የኢትዮጵያ የነገ ሰላማዊ መልክ ላይ ጉልህ ሚና ይጫወታሉ ብለዋል ።

ሁለቱም መንግስታዊ ተቋማት በአዋጅ የተሰጠ ተግባራት ቢኖራቸውም መሰል የመግባቢያ ስምምነቶች ተሻጋሪ ተግባራትን ሃላፊነት በተሞላበት መልኩ በጋራ ለማከናወን ይረዳል ብለዋል፡፡

በፀጋዬ ወንድወሰን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.