Fana: At a Speed of Life!

ኢሬቻ የፍቅር፣ የምስጋና፣ የሰላም እና የአንድነት በዓል ነው- ዶክተር አብርሀም በላይ 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢሬቻ የፍቅር፣ የይቅርታ፣ የምስጋና፣ የሰላም እና የአንድነት በዓል ነው ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሀም በላይ ገለጸ፡፡

ዶክተር አብርሀም በላይ የዘንድሮውን ኢሬቻ በዓል አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ ̎መልካም የኢሬቻ በዓል፣ ኢሬቻ የፍቅር፣ የይቅርታ፣ የምስጋና፣ የሰላም እና የአንድነት በዓል ነው̎ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በዓሉ  ̎ወንድማማችነታችንና ህብረታችን የሚጠናከርበት ይሁንልን”  ሲሉም በመልዕክታቸው ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ የኢሬቻ በዓል አከባበር በተለያዩ ዝግጅቶች በሁሉም ክፍለ ከተሞች እየተከበረ ነው፡፡

በዓሉ የፖለቲካ መልዕክት የሚተላለፍበት ሳይሆን ለፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት በመሆኑ ወጣቶች ባህላዊና ትውፊታዊ ስርዓቱን ጠብቀው ማክበር እንዳለባቸው መልዕክትም ተላልፏል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.