Fana: At a Speed of Life!

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ፋሲል ከነማ አዳማ ከተማን 2 ለ 1አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ፋሲል ከነማ አዳማ ከተማን 2 ለ1  በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

በባህርዳር ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ፍቃዱ አለሙ የፋሲልን የማሸነፊያ ሁለት ግቦች ሲያስቆጥር  ÷ አሜ ሙሃመድ  ደግሞ የአዳማ ከተማን ብቸኛ ግብ አስቆጥሯል፡፡

በጨዋታው በክረምት ዝውውር አዳማ ከተማን የተቀላቀለው ዊሊያም ሰሎሞን እና የፋሲል ከነማው አጥቂ ሽመክት ጉግሳ ባሳዩት ያልተገባ ባህሪ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብተዋል፡፡

አፄዎቹ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ከአፍሪካ ሻምፒንስ ሊግ ጨዋታ መልስ በፕሪሚየርሊጉ የመጀመሪያቸውን  ሶስት ነጥብ  ማግኘት ችለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.