Fana: At a Speed of Life!

ሀገራዊ ምክክሩ የኢትዮጵያን አንገብጋቢ ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል መሆን አለበት- ከፍተኛ አመራሮች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ስር የሰደዱ አንገብጋቢ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል መሆን እንዳለበት ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ገለጹ፡፡

የክልል ርዕሳነ-መስተዳድሮች እና ከፍተኛ አመራሮች ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ባቀረበው ስትራቴጂክ ዕቅድ እና አበይት የስራ ተግባራት ላይ ዛሬ ተወያይተዋል፡፡

ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ውጤታማ ሆኖ ችግሮችን በየደረጃው ለመፍታት እንዲችል የሁሉም ኢትዮጵያዊ ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ ሚና እንዳለው በመድረኩ ተገልጿል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ  ታገሠ ጫፎ በዚሁ ወቅት፥ ኮሚሽኑ የሀገሪቱን ቁልፍ ችግሮች ለመፍታት ትልቅ ተስፋ የተጣለበት በመሆኑ በፍጥነት ወደ ሥራ መግባት እንዳለበት አሳስበዋል።

ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ፣ የጋራ ማንነት ለመገንባት እና ቅቡልነት ያለው ሀገረ-መንግስት እንዲኖር ሀገራዊ ምክክሩ ወሳኝ ሚና እንዳለው መግለጣቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በበኩላቸው፥ የሀገራዊ ምክክሩ ዋና ተዋናይ ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ምክክሩ ውጤታማ እንዲሆን ገዥው ፓርቲ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ የገለጹት ደግሞ  የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ናቸው፡፡

የክልል ርዕሳነ-መስተዳድሮችም የዜጎችን ችግርች በዘላቂነት ለመፍታት እምነት የተጣለበት ሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማ እንዲሆን ድጋፍ ለማድረግ ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.