Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት አራት ዓመታት 4 ቢሊየን የቡና ችግኞች ተተክለዋል – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ባለፉት አራት ዓመታት በቡና ልማት የተከናወነው ስራ የምርቱን የወጪ ንግድ መጠን እንዳሳደገው የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስሰር ገፃቸው ላይ እንዳስታወቁት፥ ከአራት ዓመት በፊት የክልሉ መንግስት የነቀምቴ የቡና ስምምነት የተሰኘ ተነሳሽነትን በማፅደቅ ወደ ስራ ገብቷል።

ይህንንም ተከትሎ 4 ቢሊየን የቡና ችግኝ መትከል እንደተቻለ ነው የጠቆሙት።

ይህም የቡና የወጪ ንግድን ማሳደጉን አቶ ሽመልስ ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ በ2014 በጀት ዓመት ለውጭ ገበያ ካቀረበችው 300 ሺህ ቶን ቡና 1 ነጥብ 42 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ አግኝታለች።

ይህም ከቀደመው በጀት ዓመት ገቢ ጋር ሲነፃፀር በ21 በመቶ ወይም በ48 ሺህ ቶን ጭማሪ አለው።

በዘንድሮ በጀት ዓመትም ሀገሪቱ 2 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ከቡና የወጪ ንግድ ለማግኘት ታቅዷል ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.