Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ-ቻይና ወዳጅነት ይበልጥ እንዲጠናከር ብልፅግና ፓርቲ አበክሮ ይሰራል – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 4 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ዚሀዎ ዚሁዋን ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በርካታ ጉዳዮችን ያነሱ ሲሆን የጋራ ተጠቃሚነትን ለማስፋት፣ የሁለቱን ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር እንዲሁም የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስፋት ዙሪያ መክረዋል።

አቶ አደም ፋራህ የኢትዮ-ቻይና ዘመናትን የተሻገረ ወዳጅነት ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ብልፅግና ፓርቲ አበክሮ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

በተለይም ድህነትን በመቅረፍ፣ የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂን በማጠናከር እንዲሁም የወጪ ገቢ ንግድ አማራጮችን ለማስፋት ቻይና ቁልፍ አጋር ሆና እንደምትቀጥል ያላቸውን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በበርካታ ተግዳሮቶች ውስጥ እያለፈችም ቢሆን በተለያዩ መስኮች ስኬቶችን እያስመዘገበች እንደምትገኝ የገለፁት አቶ አደም፥ ለዚህ ስኬት መመዝገብ የፓርቲውፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ ጠንካራ የመሪነት ብቃት ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት ጠቅሰዋል፡፡

ከሁለቱ ሀገራት መንግስታዊ ግንኙነት በተጨማሪ በፓርቲ ደረጃ የብልፅግና ፓርቲ እና የቻይናው ኮሚዩኒስት ፓርቲ ግንኙነት እንዲጠናከር ብልፅግና ከፍተኛ ፍላጎት አለው ማለታቸውን ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዚሀዎ ዚሁዋን በበኩላቸው ኢትዮጵያ የቻይና ጠንካራ ስትራቴጂክ አጋር መሆኗን ጠቅሰው፥ ይህ ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲያድግ መንግስታቸው አበክሮ እንደሚሰራ አስረድተዋል፡፡

በብልፅግና ፓርቲ መንግስት መሪነት ለተፈፀሙ ስኬቶች በሙሉ ከፍ ያለ እውቅና እንደሚሰጡ በመግለጽም፥ ፓርቲው እጅግ ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉ የሪፎርም ሀሳቦች መፍለቂያ እየሆነ መምጣቱ ተጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.