Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ በኪየቭ የድሮን ጥቃት መፈጸሟ ተሰማ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 7 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ የድሮን ጥቃት መፈጸሟን የከተማዋ ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡

ጥቃቱ “ካምካዜ” በተሰኘ ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) የተፈጸመ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

በዛሬው ዕለት በከተማዋ በተፈጸመው ጥቃትም በተለያዩ አካባቢዎች ፍንዳታዎች መከሰታቸውን አርቲ ዘግቧል፡፡

በማዕከላዊ ኪየቭ አካባቢየተፈጸመው የድሮን ጥቃት ወታደራዊ መሰረተ ልማቶችን ኢላማ ያደረገ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በጥቃቱ የደረሰው ጉዳት ዝርዝር እስካሁን አለመገለጹም በዘገባው ተመላክቷል፡፡

ሩሲያ ከአንድ ሳምንት በፊት በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ በሚሳኤል ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት ማድረሷ ይታወሳል፡፡

ጥቃቱን ተከትሎም የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል ሀገራት ለዩክሬን የሚያደርጉትን ፀረ ሚሳኤል መሳሪያ ድጋፍ እንደሚያሳድጉ ገልጸዋል፡፡

አሁን ላይም ሞስኮ እና ኪየቭ በዩክሬኗ ዶኔስክ ከተማ አቅራቢያ ከባድ ጦርነት እያካሄዱ መሆኑን መረጃዎች አመላክተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.