Fana: At a Speed of Life!

ኢራን በአውሮፓ ህብረት ተጠሪ ተቋማትና ግለሰቦች ላይ ማዕቀብ ጣለች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢራን ሽብርተኝነትን ይደግፋሉ ባለቻቸው የአውሮፓ ህብረት ተጠሪ ተቋማትና ግለሰቦች ማዕቀብ ጣለች፡፡

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሁሴን አሚር አብዱላሂያን እንደገለፁት÷ ማዕቀብ የተጣለባቸው ተቋማትና ግለሰቦች ሽብርተኝነትን እና አሸባሪዎችን የሚደግፉ ናቸው።

ከዚህ ባለፈም በኢራናውያን ላይ ጥላቻን ጨምሮ የስም ማጥፋት ዘመቻ፣ ሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲፈጸም የቀሰቀሱ ብሎም ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር ያነሳሱ ናቸው ብለዋል፡፡

ማዕቀቡ በተለይም የአውሮፓ ህብረት ጥቅምት 17 ቀን በኢራን ላይ ለጣለው ማዕቀብ እና ላቀረበው መሰረተ ቢስ ውንጀላ የአፀፋ ምላሽ ለመስጠት ያለመ ስለመሆኑ ነው የተናገሩት፡፡

ህብረቱ በኢራን ላይ የጣለው ማዕቀብም የአውሮፓ ህብረት በኢራን የውስጥ ጉዳይ ላይ ግልፅ ጣልቃ ገብነቱን የሚያሳይ ነው ብለዋል የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩ፡፡

ኢራን በጥቁር መዝገብ ውስጥ ያካተተቻቸው ግለሰቦች ወደ ኢራን ለመግባት የተከለከሉ ሲሆን በኢራን ውስጥ ያሉ ንብረቶቻቸው ለኢራን መንግስት እንደሚተላለፉ ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡

ማዕቀብ የተጣለባቸው ተቋማት የነጻዋ ኢራን ወዳጆች፣ ዓለም አቀፉ ፍትህ አፈላላጊ ኮሚቴን ጨምሮ ከሰብአዊ መብት ጥሰት ጋር በታያያዘ የሚሰሩ ተቋማት ሲሆኑ፥ የአውሮፓ ህብረት አባልን ጨምሮ የየተቋማቱ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎችም በግለሰብ ደረጃ ማዕቀቡ ተጥሎባቸዋል።

ናቸውቀደም ሲል ኢራን ሽብርተኝነትን ይደግፋሉ ባላቻቸው የብሪታኒያ ተቋማትና ዜጎች ላይ ማዕቀብ መጣሏን ፕረስ ቲቪ በዘገባው አስታውሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.