ሩሲያ የሰላም ስምምነቱ ለኢትዮጵያ ሰላምና ብልጽግና መሰረት የሚጥል መሆኑን ገለጸች
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ የፌዴራል መንግስትና ህወሓት የተፈራረሙት የሰላም ስምምነት ለኢትዮጵያ ሰላምና ብልጽግና መሰረት የሚጥል መሆኑን ገለጸች።
የሩሲያ ኤምባሲ በኢትዮጵያ ባወጣው መግለጫ ÷ በፌዴራል መንግሥት እና በህወሓት መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት አድንቋል፡፡
ስምምነቱ ለኢትዮጵያ ሰላምና ብልጽግና ጠንካራ መሰረት ከመጣሉ ባሻገር የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለማቋቋም እንደሚያስችል ኤምባሲው አመላክቷል፡፡