Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ እና አፍሪካ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ጥምረት የምክክር ጉባኤ በኬፕታውን እተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ጥምረት እና የአፍሪካ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ጥምረት የምክክር ጉባኤ በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን እተካሄደ ነው፡፡

ጉባኤው በተለይም በፈጠራና ቴክኖሎጂ አጀንዳዎች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚመክር ተመላክቷል፡፡

የምክክር ጉባኤው የምርምር የልቀት ማዕከላትን በቡድን ማቋቋምና ማጠናከር ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑ ነው የተገለጸው፡

በመድረኩ የደቡብ-ደቡብ እንዲሁም የሰሜን-ደቡብ ግንኙነትን ታሳቢ በማድረግ የሳይንስ ልቀት ትብብር ስለመመስረት እና የምርምር ልቀትን ስለማጠናከር ውይይት ተካሂዷል፡፡

በዚህም ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣት ተመራማሪዎች ሳይንሳዊ እድገትና የምርምር ክህሎት የሚያሳድግ፣ ለከፍተኛና መሪ ተመራማሪዎችም ልምዳቸውን የሚያካፍሉበት ከፍተኛ የምርምር ተቋማትን ስለመገንባት ውይይቱ ዳስሷል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ፣ ተደራሽና አካታች የሳይንስና ቴክኖሎጂ የምርምር ተቋማትን በአውሮፓ ኅብረትና በአፍሪካ ኅብረት ድጋፍ ማጠናከርና በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የአውሮፓ- አፍሪካ ተማሪዎች ግንኙነትን ማጠናከርም የጉባኤው ተሳታፊዎች ያነሷቸው ነጥቦች ናቸው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.