Fana: At a Speed of Life!

በተለያዩ ሀገራት በተደረጉ የማራቶን ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 28፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ ሀገራት በተደረጉ የማራቶን ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡

በአሜሪካ በተካሄደው የኒውዮርክ ማራቶን በወንዶች አትሌት ሹራ ቂጣታ 2 ሰዓት ከ8 ደቂቃ ከ54 ሰከንድ በመግባት አሻነፊ ሰሆን፥ በሴቶች አትሌት ጎቲቶም ገብረስላሴ 2 ሰዓት ከ23 ደቂቃ ከ39 ሰከንድ በመግባት 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡

በፖርቹጋል ፖርቶ በተካሄደው ማራቶን ደግሞ አትሌት አብራራው ምስጋናው 2 ሰዓት ከ11 ደቂቃ ከ29 ሰከንድ በመግባት 2ኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ፥ አትሌት ሀይማኖት አለሙ 3ኛ፣ አትሌት ዳዲ ያሚ 4ኛ እንዲሁም አትሌት ጫሌ ደቻሳ 5ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል፡፡

በቱርክ ኢስታንቡል በተካሄደ የማራቶን ውድድር ደግሞ በሴቶች አትሌት ሲጫሌ ደላሳ 2 ሰዓት ከ25 ደቂቃ ከ54 ሰከንድ በመግባት ቀዳሚ ስትሆን አትሌት መሰለች ፀጋየ 2ኛ እንዲሁም አትሌት እታለማሁ ስንታየሁ 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል፡፡

በስዊዘርላንድ ጀኔቭ በተካሄደው የ20 ኪሎ ሜትር ውድድር አትሌት ሄለን በቀለ 1 ሰዓት ከ6 ደቂቃ ከ3 ሰከንድ በመግባት ቀዳሚ ሆናለች።

በስፔን ዓለም አቀፍ ሀገር አቋራጭ ውድድር በወንዶች አትሌት አዲሱ ይሁኔ ቀዳሚ ሲሆን፥ በሴቶች አትሌት መሰሉ በርሄ 2ኛ እንዲሁም አትሌት እታለማሁ ስንታየሁ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ማጠናቀቃቸውን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.