Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ የፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ለሰላም ስምምነቱ ተፈፃሚነት ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ የፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሰላም ስምምነቱ በመርህ ደረጃ ተፈፃሚ እንዲሆን ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጠየቀ፡፡

ምክር ቤቱ ዛሬ በሰጠው መግለጫ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት ለሀገራችን እድገትና ልማት ወሳኝ መሆኑን በማንሳት ስምምነቱን በመርህ ደረጃ እንደሚደግፍ ገልጿል፡፡

የጋራ ምክር ቤቱ ለተደረሰው የሰላም ስምምነት ተግባራዊነት እንደሚሰራ የገለፀ ሲሆን መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እና የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ለሰላም ስምምነቱ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ የድርሻውን እንዲወጣም ጥሪ አቅርቧል።

አፍሪካውያን የራሳችንን ችግር በራሳችን ለመፍታት ለተደረገው ጥረት እውቅናና ምስጋና የሰጠው የጋራ ምክር ቤቱ መግለጫ የትግራይን ክልል መልሶ ለማቋቋምና የተገኘውን ሰላም ለማስጠበቅ ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቋል።

በምንተስኖት ሙሉጌታ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.