Fana: At a Speed of Life!

የኤፍ . ቢ. አይ የዓለም አቀፍ ኦፕሬሽን ዲቪዥን ም/ዳይሬክተር በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሥራ ጉብኝት አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የአሜሪካ የአሜሪካ የፌደራል ምርመራ ቢሮ (ኤፍ. ቢ. አይ) የዓለም አቀፍ ኦፕሬሽን ዲቪዥን ምክትል ዳይሬክተር ሬይሞንድ ዱዳ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት የሥራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

በጉብኝቱ በኢትዮጵያ የአሜሪካ መንግሥት ጉዳይ ፈጻሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰንም ተገኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ባለፉት አራት ዓመታት የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎችን አስረድተዋል፡፡

ሬይሞንድ ዱዳ በበኩላቸው÷ ኤፍ.ቢ.አይ በድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ላይ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጋር በትብብር እየሠራ ነው ብለዋል፡፡

ለአብነትም÷ በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ሽብርተኝነትን በመከላከል እና በመሳሰሉት ዘርፎች በጥምረት እየሠሩ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

ሁለቱ ተቋማት በቀጣይ ግንኙነታቸውን የበለጠ አጠናክረው በሰላምና ደኅንነትላይ አብረው ለመሥራት መስማማታቸውን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

ኤፍ.ቢ.አይ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስን በአቅም ግንባታ እና የፎረንሲክ ዲፓርትመንቱንም በቁስ እንደሚደግፍ አረጋግጠዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.