Fana: At a Speed of Life!

የዛሬ 7ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል

 

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 1 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዛሬ 7ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል::

በዚህም 10 ሰዓት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወልቂጤ ከተማ ባደረጉት ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስን ግቦች አማኑኤል ገብረሚካኤልና እስማኤል ኦሮ-አጎሮ ሲያስቆጥሩ የወልቂጤ ከተማን ሁለቱንም ግቦች አቡበከር ሳኒ አስቆጥሯል፡፡

በተመሳሳይ 1 ሰዓት ላይ ድሬዳዋ ከተማና መቻል ባደረጉት ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

የመቻልን ግብ ያሬድ ታደሠ ሲያስቆጥር የድሬዳዋ ከተማን ግብ ሳሙኤል ሳሊሶ አስቆጥሯል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.