Fana: At a Speed of Life!

ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አገልግሎቱን የሚመጥን ትኩረት አላገኘም ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ኃብት ልማት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሪፈራልና የማስተማሪያ ሆስፒታል የሚሰጠውን አገልግሎት የሚመጥን ትኩረት አለማግኘቱን ገልጿል።
 
የቋሚ ኮሚቴው አባላት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስር የሚገኙ የተለያዩ ኮሌጆች እና ተቋማትን የስራ እንቅስቃሴ በመስክ ምልከታ ገምግመዋል፡፡
 
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ÷በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስር የሚገኘው ጥቁር አንበሳ ሪፈራል ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እየሰጠ ካለው አገልግሎትና የምርም ስራ አንፃር በበጀትም ሆነ በተለያዩ ድጋፎች ተመጣጣኝ ትኩረት ሊያገኝ ይገባል ብለዋል።
 
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር አንዷለም ደነቀ በበኩላቸው÷ ሆስፒታሉ በዓመት 500 ሺህ ተመላላሽ እና 20 ሺህ ተኝተው የሚታከሙ ህሙማንን እያገለገለ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
 
ይሁን እንጂ ሆስፒታሉ ባለው የበጀት እጥረት እና የቦታ ጥበት መቸገራቸውን ነው የተናገሩት፡፡
 
ዶክተር ነገሪ ሌንጮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስር የሚገኙት የትምህርት እና የጤና ማዕከላት ተገቢውን ትኩረት ሊያገኙ እንደሚገባ ቋሚ ኮሚቴው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር እንደሚሰራ መግለጻቸውን የም/ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.