Fana: At a Speed of Life!

17ኛው የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባኤ ለኢትዮጵያ በርካታ ትሩፋቶችን ይዞ እንደሚመጣ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የምታስተናግደው 17ኛው የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባዔ በርካታ ትሩፋቶችን ይዞ እንደሚመጣ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ በ17ኛው የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባዔ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም ኢትዮጵያ በርካታ የቱሪስት መዳረሻዎች ያሏት ሀገር መሆኗን አንስተው÷ ጉባዔው በርካታ ጥቅሞችን ይዞላት እንደሚመጣ ተናግረዋል።

በ17ኛው የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባኤ ከመላው ዓለም የተውጣጡ እስከ 2 ሺህ 500 ተሳታፊዎች ይሳተፋሉ ተብሏል።

ጉባዔው ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ ሀገራት ጠቃሜታው የጎላ መሆኑንም ነው ሚኒስትር ዴኤታዋ የገለጹት።

ኢትዮጵያ በ2025 ካቀደችው ዲጂታል ኢኮኖሚ ግብ ለመድረስ ጉባዔው የራሱ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡

ጉባዔው ከፈረንጆቹ ከህዳር 19 እስከ 23 ቀን በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ በመግለጫው ተመላክቷል፡፡

በፍቅርተ ከበደ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.