Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ በክልል ደረጃ የዘንድሮውን የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በምስራቅ ሸዋ ዞን ዋቄ ሚኣ ቀበሌ በይፋ አስጀመሩ።

በክልሉ በበጋ ስንዴ መስኖ ልማት ከ1 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት ለመሸፈን እየተሰራ ይገኛል ።

በምስራቅ ሸዋ ዞን በሚገኙ 10 ወረዳዎች በ136 ቀበሌዎች ላይ የማሳ ዝግጅት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

በዚህም በዞኑ 200 ሺህ ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ለመሸፈን እየተሰራ መሆኑንና እስከ አሁን በዞኑ ከ26 ሺህ ሄክታር በላይ በዘር መሸፈኑ ነው የተገለጸው ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.