የህፃናትን በሽታ የመከላከል አቅም ለማሳደግ የሚረዱ መንገዶች
አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ህጻናት በቀላሉ እንዳይታመሙ በሽታ የመከላከል አቅማቸው መጎልበት አለበት::
ይህንንም ለማድረግ ደግሞ መሠረታዊ መርሆዎችን ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡
እነሱም ጡት ማጥባት፦ ቢያንስ ለመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ጨቅላ ህጻናትን ጡት ብቻ ማጥባት የራሱ የሆኑ ጠቀሜታዎችን ይሰጣል::
በየጊዜው እጅ መታጠብ፦ ህፃናትን ሲያስነጥሱ፣ ሲያስሉ እና ወደ መጸዳጃ ቤት ከሄዱ በኋላ እጃቸውን ለመታጠብ ጊዜ እንዲወስዱ ማስተማር፣ እጅን በሞቀ ውሃ እና ሳሙና ቢያንስ ለ20 ሰከንድ መታጠብ ባክቴሪያዎችን እና ቫይረሶችን ያስወግዳል፡፡
የክትባት ወቅትን አለማሳለፍ፦ በልጅነት የሚወሰዱ ክትባቶች እንደ ኩፍኝ ፣ ጉድፍ ፣ ፖሊዮ እና ሮታ ቫይረስን ስለሚከላከል የክትባት ጊዜ ፈጽሞ አያምልጣቸው::
አመጋገብን ማስተካል፦ ትክክለኛ የምግብ ምርጫ ልጅዎ በቂ ቫይታሚኖችን ማግኘቱን ለማረጋገጥ ይረዳል።
ጤናን ለመጠበቅ እና ጠንካራ የበሽታ መከላከል ስርዓትን ለመጠበቅ ቫይታሚኖች ያስፈልጋሉ።
በቂ እንቅልፍ፦ ህፃናት በሽታ የመከላከል አቅማቸው ከፍ እንዲል በቂ እንቅልፍ ማግኘት እንደሚኖርባቸው
ከጥቁር አንበሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ገፅ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።
የእንቅልፍ ሰአቱ እንደ እድሜያቸው መጠን የሚለያይ ሲሆን፥ ባለሙያዎች በሚያዙት መሰረት በቂ ሰአት እንዲተኙ ማድረግ ያስፈልጋል።