ፈረንሳይ እና አውስትራሊያ ጥሎ ማለፉን ተቀላቀሉ
አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 21 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ዋንጫው ፈረንሳይ እና አውስትራሊያ ጥሎ ማለፉን መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል።
ማምሻውን 12 ሰአት በተካሄደው ጨዋታ ፈረንሳይ በቱኒዚያ 1 ለ 0 ብትሸነፍም ምድቡን እየመራች ጥሎ ማለፉን ተቀላቅላለች።
ከዴንማርክ የተጫወተችው አውስትራሊያ 1 ለ 0 በማሸነፍ ጥሎ ማለፉን መቀላቀሏን አረጋግጣለች።