Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንትዕድሎች ዙሪያ ከአሜሪካ ባለሃብቶች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ ከአሜሪካ ባለሃብቶች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ ከዩናይትድ ስቴትስ ኢንቨስተሮች ጋር ባልተነኩ የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ መምከራቸውን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ ታሪካዊ የሚባል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን እየተገበረች እንደመሆኗም፥ ለጋራ ብልፅግና በኢትዮጵያ ህዝብና ኢኮኖሚ ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ጥረት እንዲያደርጉ አበረታትቻቸዋለሁ ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.