Fana: At a Speed of Life!

የሸኔን ቡድን የመደምሰስ ስራ ለሰራዊቱ ብቻ የሚተው አይደለም- አቶ አወሉ አብዲ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሸኔን ቡድን የመደምሰስ ስራ ለሰራዊቱ ብቻ የሚተው አይደለም ሲሉ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዲ ተናገሩ፡፡

የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ሠላም የሠፈነባት ኢትዮጵያን ለመገንባት ከኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና ከፀጥታ አካላት ጋር መክረዋል።

በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዲ ህዝብን ለማሸበር በምዕራብና ምስራቅ ወለጋ የሚንቀሳቀሰውን የሸኔ ቡድን መደምሰስ ለሠራዊቱ ብቻ የሚተው አይደለም ብለዋል፡፡

ህዝቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በትብብር ሊሰራ ይገባል ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍን የሽብር ቡድኑን አካላት አሳልፎ በመስጠት የተለመደውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በምክክሩ ፀረ ሰላም ሀይሎችን በጋራ በመታገል ሀገራችን ሙሉ በሙሉ ፊቷን ወደ ልማት እንድታዞር የማድረግ ተግባር የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሀላፊነት ነው መባሉን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.