Fana: At a Speed of Life!

ለቻን ውድድር ለ28 ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ሀገራት ሻምፒዮንሺፕ (ቻን) ለሚያደርገው ተሳትፎ ዝግጅት ለ28 ለተጫዋቾች ጥሪ ተደርጓል።

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከዚህ ቀደም 42 ተጫዋቾችን ያካተተ ጊዜያዊ የተጫዋቾች ጥሪ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

ሆኖም በድሬዳዋ እየተካሄደ በሚገኘው የፕሪሚየር ሊግ ውድድር ላይ ተገኝተው የተጫዋቾችን ወቅታዊ ብቃት እና ሁኔታ በመገምገም የተጫዋቾችን ቁጥር በመቀነስ ለ28 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል፡፡

በዚህም ፡-ግብ ጠባቂዎች
ፋሲል ገ/ሚካኤል – ባህር ዳር ከተማ
በረከት አማረ -ኢትዮጵያ ቡና
ባህሩ ነጋሽ -ቅዱስ ጊዮርጊስ
ተከላካዮች

ሱሌማን ሀሚድ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ረመዳን የሱፍ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ዓለምብርሃን ይግዛው – ፋሲል ከነማ
ጊት ጋትኩት -ሲዳማ ቡና
አስቻለው ታመነ -ፋሲል ከነማ
ምኞት ደበበ -ቅዱስ ጊዮርጊስ
ብርሃኑ በቀለ – ሃዲያ ሆሳዕና
ፈቱዲን ጀማል -ባህር ዳር ከተማ
ገዛኸኝ ደሳለኝ – ኢትዮጵያ ቡና
ሚሊዮን ሰለሞን- አዳማ ከተማ

አማካዮች

ጋቶች ፓኖም – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ይሁን እንዳሻው -ፋሲል ከነማ
ከነዓን ማርክነህ – መቻል
መስኡድ መሐመድ – አዳማ ከተማ
ታፈሰ ሰለሞን – ፋሲል ከነማ
ፉአድ ፈረጃ -ባህር ዳር ከተማ
አለልኝ አዘነ -ባህር ዳር ከተማ
ወንድማገኝ ኃይሉ- ሀዋሳ ከተማ

አጥቂዎች

ቸርነት ጉግሳ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ቢኒያም በላይ -ቅዱስ ጊዮርጊስ
ይገዙ ቦጋለ – ሲዳማ ቡና
አማኑኤል ገ/ሚካኤል – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ኪቲካ ጀማ – ኢትዮጵያ መድን ድርጅት
ዱሬሳ ሹቢሳ- ባህር ዳር ከተማ
ጌታነህ ከበደ -ወልቂጤ ከተማ

ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ሲሆኑ በቀጣዩ ቀን የጤና እና አካል ብቃት ምርመራ ከተደረገላቸው በኋላ ልምምድ እንደሚጀምሩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.