ወተር ኤይድ ኢትዮጵያ የጤና ጣቢያዎችና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት የተቋቋሙ ማእከላት የስነ ንፅህና አገልግሎታቸውን ማሻሻል የሚያስችሉ ቁሳቁሶች ድጋፍን አደረገ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 23 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ወተር ኤይድ ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ የሚገኙ የጤና ጣቢያዎች እና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት የተቋቋሙ ጊዜያዊ ማእከላትን የውሃ እና የስነ ንፅህና አገልግሎትን ማሻሻል የሚያስችሉ ቁሳቁሶች ድጋፍን አደረገ።
ድርጅቱ እነዚህ የጤና ተቋማት የቫይረሱን ወረርሽን በአግባቡ ለመግታት ያስችላቸዋል ያላቸውን እስከ 5 ሺህ ሊትር ውሃ የሚይዙ 50 ታንከሮችን ለውሃ፣ መስኖና ኤነርጂ ሚኒስቴር ዛሬ አስረክቧል።
በተጨማሪም 2 ሺህ 500 ሊትር አልኮሆል እና 1 ሺህ የንፅህና መጠበቂያ ሳሙናዎችን አበርክቷል።
በአጠቃላይ 2 ነጥብ5 ሚሊየን ብር የሚያወጡ ቁሳቁሶችን እና ሌሎች ድጋፎችን ያደረገው ድርጅቱ በቀጣይ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመግታት መሰል ድጋፎችን እንደሚያደርግም ነው ያረጋገጠው።
የውሃ፣ መስኖና ኤነርጂ ሚኒስቴር ድጋፉ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ወሳኝ ለሆኑት የጤና ተቋማት የስነ ንፅህና አገልግሎታቸውን ለማሳደግ ጠቃሚ መሆኑን በማንሳት ቫይረሱን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር እስከሚቻል ድረስ ድጋፉ እንደሚቀጥል እምነቱን ገልጿል።