Fana: At a Speed of Life!

ለሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ሂደት አስፈላጊውን ድጋፍ እናደርጋለን – ከንቲባ ከድር ጁሃር

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ሂደት ስኬታማነት አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እንደሚያደርጉ የድሬዳዋ አሥተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ገለጹ።

ኮሚሽኑ የተዛነፉ ትርክቶችና ስብራቶችን ለማንፃት እና ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር የጀመራቸው ሥራዎች አበረታች መሆናቸውንም ነው ከንቲባው የገለጹት፡፡

በሀገራዊ ጉዳይ ላይ የሚመለከታቸው ሁሉ ተወያይተው ብሔራዊ መግባባት እንዲፈጠር የኮሚሽኑ እንቅስቃሴዎች አመላካች መሆናቸውን ጠቅሰው÷ ለስኬታማነቱም ሁሉም ርብርብ ሊያደርግ እንደሚገባ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽኑ በድሬዳዋ የሁሉንም ኅብረተሰብ ክፍሎች በማካተት ያካሄዳቸው የቅደመ ዝግጅት ሥራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጸው÷ በቀጣይም ተልዕኮው እንዲሳካ አሥተዳደራቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.