Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ወደ አውሮፓ የጋዝ አቅርቦቷን በድጋሚ ልትጀምር ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በያማል- አውሮፓ የጋዝ መስመር በኩል ለአውሮፓ የጋዝ አቅርቦቷን በድጋሚ ለመጀመር መዘጋጀቷን የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ኖቫክ ተናገሩ፡፡

በአውሮፓ የጋዝ እጥረቱ እንደቀጠለ መሆኑን ያነሱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ÷በዚያ ያለው ገበያ ጠቃሚ እንደሆነ እና አቅርቦቶችን ለመቀጠል እድሉ እንዳለ ለሀገሪቱ የዜና ወኪል ተናግረዋል፡፡

የያማል- አውሮፓ የጋዝ መስመር በፖለቲካዊ ምክንያት እስካሁን አገልግሎት ሳይሰጥ መቆየቱንም ጠቅሰዋል፡፡

ሞስኮ የፖላንድ ክፍል የያማል- አውሮፓ ባለቤት በሆነው ድርጅት ላይ ማዕቀብ ከጣለች በኋላ የሀገሪቱ ዋነኛው የጋዝ አቅራቢ ጋዝፕሮም በፖላንድ በኩል ጋዝ መላክ እንደማይችል ማስታወቁን የሬውተርስ ዘገባ አመላክቷል።

በዚህ አመት ወደ አውሮፓ የሚደረገው የፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦትን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ችለናል ያሉት ኖቫክ÷ በ2022 ሞስኮ 21 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ወደ አውሮፓ ትልካለች ብለው እንደሚጠብቁም ገልጸዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.