Fana: At a Speed of Life!

የህብረተሰቡን የመልማት ፍላጎት የሚመጥን የመሰረተ ልማት ግንባታ በፍጥነት መስራት ይገባል – አቶ ደስታሌዳሞ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የህብረተሰቡን የመልማት ፍላጎት የሚመጥን የመሰረተ ልማት ግንባታ በፍጥነት መሰራት አለበት ሲሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታሌዳሞ ገለጹ፡፡
 
የሲዳማ ክልል የመሰረተ ልማት የስድስት ወር ዕቅድ አፈጻጸም ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በተገኙበት እየተገመገመ ነው፡፡
 
በመድረኩ የሲዳማ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ፍስሃ ፊቾላ እና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ብርሃኑን ጨምሮ ሌሎች የስራ ሃላፊዎች እና ባለደርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡
 
አቶ ደስታ ሌዳሞ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር ÷ የህብረተሰቡን የመልማት ፍላጎት የሚመጥን የመሰረተ ልማት ግንባታ በፍጥነት መሰራት አለበት ብለዋል።
 
ለዚህም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ መናገራቸውን ከርዕሰ መስተዳድሩ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.