Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሙስጠፌ በዱሁን ወረዳ የተገነባውን ድልድይ መርቀው ስራ አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ መሃመድ በኖጎብ ዞን ዱሁን ወረዳ የተገነባውን ድልድይ መርቀው አገልግሎት አስጀምረዋል፡፡

ድልድዩ በሶማሌ ክልል የመስኖና ተፋሰስ ልማት ቢሮ የተገነባ ሲሆን÷ ግንባታው ላለፉት ሶስት ዓመታት ሲካሄድ መቆየቱ ተጠቁሟል፡፡

የዱሁን ወረዳ ነዋሪዎች የክልሉ መንግስት የወረዳውን ህዝቡ የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ በተግባር እያከናወናቸው ለሚገኙ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።

የዱሁን ወረዳ ድልድይ የኖጎብ፣ ኤረር፣ ሸበሌና ጀረር ዞን ነዋሪዎችን ግኑኝነትና የንግድ እንቅስቃሴዎችን ማፋጠን የሚያስችል መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በሌላ በኩል አቶ ሙስጠፌ÷ በ60 ሚልየን ብር ወጪ በምስራቅ ኢመይ ወረዳ የተገነባውን ከ25 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የንፁህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.