Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልል እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊ፣ ክልላዊ ፖለቲካዊ ሁኔታዎች፣ ሠላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው።

በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ፖለቲካዊ አዝማሚያዎች ላይ የጋራ አረዳድ በመፍጠር÷ የተጀመረው የሰላም፣ የልማትና የዲሞክራሲ ግንባታ ሂደት እንዲጠናከርና አመራሩ ሚናውን በላቀ ደረጃ እንዲወጣ የመድረኩ ፋይዳ የጎላ መሆኑ ተገልጿል።

አቶ አደም ፋራህ ሀገራዊና ቀጣናዊ ወቅታዊ ፖለቲካዊ አዝማሚያዎችን፣ ለዘላቂ ሠላም ግንባታ የተፈጠሩ ምቹ ሁኔታዎችንና ስጋቶችን በተመለከተ መነሻ ሐሳብ ማቅረባቸውን የሐረሪ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

አቶ ኦርዲን በድሪ የክልሉን አቶ ከድር ጁሃር ደግሞ የአስተዳደሩን÷ ወቅታዊ ፖለቲካዊ አዝማሚያዎች፣ የሠላምና የፀጥታ ሁኔታዎችን አስመልክተው መነሻ ሐሳብ አቅርበዋል፡፡

ከውይይቱ በኋላ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ የሕዝብ ተጠቃሚነት፣ ሀገራዊ አንድነትና ወንድማማችነትን በጋራ አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችል አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ይጠበቃል፡፡

በመድረኩ÷ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የፓርቲው ዋና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አደም ፋራህ ፣ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳድር ከንቲባ ከድር ጁሃር፣ የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካና ርዕዮተ ዓለም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አብርሃም አለኸኝ፣ የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ሳዳት ነሻ እንዲሁም የሐረሪ ክልል እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.