Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በጋራ ለመስራት ተስማሙ፡፡

ስምምነቱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና በመግባት መስራት የሚያስችለው ነው ተብሏል፡፡

የመግባቢያ ስምምነት ሰነዱን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሆል ሴል ባንኪንግ ምክትል ፕሬዚዳንት ሙሉነህ ለማ እንዲሁም የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አክሊሉ ታደሰ ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በነፃ የንግድ ቀጠናው የሚሰጠውን የፋይናንስ አገልግሎት ዘርፍ በማሳለጥ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣና፣ ኢንቨስት ለሚያደርጉ ባለሀብቶችም ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ያስችለዋል መባሉን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.