Fana: At a Speed of Life!

አፍሪካን የ“ዓለም የዳቦ ቅርጫት” ለማድረግ 10 ቢሊየን ዶላር ተመደበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ልማት ባንክ ግሩፕ በቀጣይ አምሥት ዓመታት አኅጉሪቱን የ“ዓለም የዳቦ ቅርጫት”ለማድረግ 10 ቢሊየን ዶላር መደበ፡፡

ባንኩ በአፍሪካ የረሃብ ድምፅ እንዳይሠማ እና አኅጉሪቷ ራሷን በምግብ ችላ ቀሪውንም ዓለም እንድትመግብ ርዕይ ሠንቆ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የአፍሪካ ልማት ባንክ ግሩፕ ዕቅዱን ይፋ ያደረገው በፕሬዚዳንቱ ዶክተር አኪንዉሚ አዴሲና በኩል በ”ዳካር 2 የአፍሪካ የምግብ ጉባዔ ላይ ነው፡፡

ጉባዔው ከሴኔጋሏ ርዕሠ-መዲና ዳካር በምሥራቅ በኩል ዲያምኒያያዲዮ መካሄዱም ታውቋል፡፡

ዶክተር አኪንዉሚ አዴሲና ÷ በጉባዔው ላይ ለተካፈሉ ከ34 በላይ የሀገራት መሪዎች ፣ 70 ሚኒስትሮች ፣ ለግሉ ዘርፍ ተዋንያን፣ ለአርሶ አደሮች፣ ለልማት አጋሮች እና ለድርጅት ሥራ አሥፈፃሚዎች አፍሪካ በምግብ እና በግብርና ላይ ሠርታ ለውጥ እንድታመጣ የበኩላቸውን እንዲወጡ አስገንዝበዋል።

በጥምረት በግብርናው ዘርፍ ላይ እንዲሠሩ እና አኅጉራዊውን የግብርና ትራንስፎርሜሽን ዕውን እንዲያደርጉም ጠይቀዋል፡፡

አፍሪካ ከራሷ አልፋ ዓለምን መመገብ የምትችል የዳቦ ቅርጫት የመሆን ዐቅም ያላት አኅጉር መሆን እንደምትችልም ነው በመክፈቻ መርሐ-ግብሩ ላይ የተናገሩት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.