Fana: At a Speed of Life!

የዜጎች ፍትሃዊ የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘት አለባቸው – አቶ አገኘሁ ተሻገር

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ግንኙነት በመፍጠር የዜጎችን ፍትሃዊ የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች መመለስ አለብን ሲሉ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት እና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ውይይት እየተካሄደ ነው።

የውይይት መድረኩ በቀጣይ ሕገ-መንግስታዊነትን ፣ የዴሞክራሲ ሥርዓትን እና ዘላቂ ሠላምን በሀገሪቱ ለማስፈን ያለመ ነው ተብሏል።

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ከ4 ዓመት በፊት ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ የፖሊሲ ማሻሻያዎች ማድረጉን እና የነበረበትን ክፍተት መሙላቱን አስታውቋል፡፡

አቶ አገኘሁ ተሻገር ÷ ምክር ቤቱ ከሀገራዊ እና መንግስታዊ ተልዕኮ ባለፈ ከሲቪል ማኅበረሰቡ ጋር በትብብር እና በቅንጅት ይሠራል ብለዋል።

በምንይችል አዘዘው እና ሲሳይ ዱላ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.